የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ70 አቅመ ደካማ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ድጋፍ ተደረገ።

(ሚያዝያ 25/2016 ዓ.ም)፦ ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት በአርባምንጭ ከተማ ለሚገኙ ሰባ (70) አቅመ ደካሞች ለእያንዳንዳቸው 1 ዶሮ ፣ 10 ኪሎ የስንዴ ዱቄት ፣ ዘይት እና 10 እንቁላል ድጋፍ አደረገ። 

የተደረገላቸዉን ድጋፍ በአካል ቀርበዉ የተቀበሉ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ አባላት ከመንግስትና ከድሃዉ  ጎን በመሆን ድርጅቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት በአርባምንጭ ከተማና አከባቢዉ በመንግስት አቅም የማይሸፈኑ የልማት ተግባራት ከአጋቾቹ ጋር በመተባበር እያከናወነ ይገኛል። ድርጅታችን በአርባምንጭ ከተማ ለሚገኙ ለ100 ቤተሰቦች የ2016 ሙሉ የጤና መድህን ወጪ የሸፈነላቸቁ ሲሆን በየበዓላቱ ለድሆች በዓይነት ድጋፍ ፣ የአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ መርሐግብር ድጋፍ ፣ ለድሆች የአልባሳት ድጋፍ ፣ የማዕድ ማጋራት ፣ በጋሞ ዞን ጤና ልማት የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ ፣