ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ አቅም የሌላቸዉ ወገኖች ማዕድ አጋራ።

ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ አቅም የሌላቸዉ ወገኖች ማዕድ አጋራ።

(ጥቅምት 24/2016 ዓ.ም ፤ አርባምንጭ) ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በብዙ መቶ ሺህዎች ገንዘብ ወጪ በማድረግ በተለያዩ ጊዜያት በአርባምንጭ ማዕከሉ ድሆችን የመመገብ መርሐግብር ሲያከናዉን ቆይቷል። ድርጅቱ ይህንን ሰብአዊ ፕሮግራም በማጠናከር በአርባምንጭ ከተማ አቅም ለሌላቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሐግብር አከናዉኗል። 

ድርጅታችን በራሱ ሙሉ ወጪ 30 የድሃ ድሃ ቤተሰብ ልጆች  ምገባና መዋዕል ሕጻናት ትምህርት በመስጠት የነገ ሀገር ተረካቢዎች ማብቃት ሥራዎች ጭምር እያከናወነ ይገኛል።

ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ድሆች ማዕድ ማጋራት ፣ አልባሳት ድጋፍ ፣ ትምህርት እና ለአካል ጉዳተኞች አጋዥ ዊልቼር ድጋፍ በሚሊዮኖች የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ በአርባምንጭ ከተማ መንግስትና ሕዝብ እያገዘ ይገኛል።